ሰበር ዜና፡ የ አስገደ ገብረስላሴ ልጅ ቶርቸር እየተፈፀመበት ነው አብረሃ ደስታ፣ ከመቀሌ

 

አሕፈሮም አስገደ (የኣስገደ ገብረስላሴ ልጅ) መታሰሩንና ቤተሰቦቹ እንዲያዩት እንዳልተፈቀደላቸው ፅፌ ነበር። ከሰዓታት በፊት ግን አባቱ ኣቶ አስገደ ገብረስላሴ ልጁ እንዲያሳዩት የፖሊስ ኣዛዦችንEthiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele ይጠይቃል። ፖሊሱ (የቀዳማይ ወያነ ወረዳ ኣዛዥ ኮነሬል ….. ዋና ኢንስፔክተር) ልጁ ወደ ሌላ እስርቤት መዛወሩ (ከማስፈራርያ ጋር) ነግሮታል።

“ወደ የትኛው እስርቤት ተዛወረ ?” ብሎ ሲጠይቅ ኣስደንጋጭ መልስ ተሰጠው፤ “ወደ ባዶ ሽዱሽተ እሰርቤት” የሚል። “ባዶ ሽዱሽተ” (06 ዜሮ ስድስት) እስርቤት የህወሓት እስርቤት ነው። ህወሓቶች ተሰቃይቶ መረጃ እንዲሰጥ የሚፈለግ ሰው ሲገኝ ወደ “ባዶ ሽዱሽተ” ይወሰዳል። ከዛ ቶርቸር ይፈፀምበታል፤ በመጨረሻም ይገደላል (ይረሸናል)። “ባዶ ሽዱሽተ” የስቃይ እስርቤት ነው። ይሄ እስርቤት ህወሓቶች ጫካ እያሉ የሚጠቀሙበት የነበረ ነው።

እስካሁን ድረስ ይሄ እስርቤት መኖሩ ገርሞኛል። (ህወሓቶች ስልጣን ይዘው እያሉም …. ለምን ኣስፈለገ???) ልጁ ቤተሰቦቹና የሕግ ኣማካሪው እንዲያዩት ያልተፈቀደው በቀዳማይ ወያነ ወረዳ ማረምያ ቤት ስላልነበረ ነው። ወላጆቹ ይሉክለት የነበረው ምግብ (ካለፈው እሮብ ጀምሮ) ለልጁ ሳይሰጥ በእስርቤቱ ተበላሽቶ ይገኛል።

ሰው እንዲያየው ያልተፈቀደው ያለበት እስርቤት (ባዶ ሽድሽተ) ሕጋዊ ስላልሆነ ነው። በመቀለ ከተማ የሚገኙ ሕጋዊ እስርቤቶች ሰባት ብቻ ናቸው። “ ባዶ ሽድሽተ” ግን ሕጋዊ አይደለም፤ ፍርድቤት አያውቀውም። ወደዛ የገቡ እስረኞ ች ያለፍርድ ቶርቸር (ግርፋት) ይደርሳቸዋል (በቶርቸር ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል)።

ባጭሩ “ ባዶ ሽድሽተ” ለቶርቸር ብቻ የተዘጋጀ ሕቡእ (hidden) እስርቤት ነው። አንዳንድ ስለ እስርቤቱ (እስካሁን መኖር የሚያውቁ) የመቐለ ኗሪዎች “ቤርሙዳ” ብለው ይጠሩታል: “እዛ እስርቤት የገባ መውጭያ የለውም” ለማለት። ። ይሄን ሕቡእ፣ ንፁህ ዜጎች የሚሰቃዩበት እስርቤት (ባዶ ሽድሽተ) ሚላኖ ሆተል አከባቢ ከባሎኒ ስታዲዮም ወደ ምስራቅ 100 ሜትር ገባ ብሎ፣ ጀወርግስ ቤተክርስትያን፣ ወደ እንዳየሱስ (ኣሪድ ግቢ መቐለ ዩኒቨርስቲ) ጠጋ ብሎ በሚገኝ (ተራራና ሸለቆ የበዛበት) ጫካ ያለበት ስፍራ ሲሆን underground prison ነው።

በኣሁኑ ሰዓት እየተገረፈ እንዳለ መስማቴ ኣሳዝኖኛል። ለምን underground እስርቤት? ለምን ሕጋዊ ያልሆነ እስርቤት?

አሳዛኝ ነው።

SOURCE. ECADFORUM

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s