ዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ስርአት መለወጥ አለበት አለ

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ስርአት ካልተለወጠ፤ የኢትዮጵያ እድገት ግቡን መምታቱ አጠራጣሪ ነው ሲል የዓለም ባንክ አስጠነቀቀ።

የዓለም ባንክ ባለፈው ሳምንት በሂልተን ሆቴል በለቀቀው፤ “ሁለተኛ ደረጃ ት/ት በኢትዮጵያ፤ እድገትና ለውትን ለማገዝ” (Secondary Education in Ethiopia: Supporting Growth and Transformation ) የተሰኘ ጥናት እንደገለጸው፤ ኢትዮጵያ የጠቅላላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ስርአቷና ካላሻሻለች፤ በ2025 መካከለኛ የምጣኔ ሀብት (ወይም ኢኮኖሚ) ወዳላቸው አገሮች ደረጃ ማደግ መቻሏ የማይታሰብ ነው ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ኢትዮጵያ መካከለኛ የኢኮኖሚ እድግት ደረጃ ላይ ለመድረስ የምታደርገው ጥረት አበረታች መሆኑን የጠቀሰው ጥናት፤ ኢትዮጵያ በ2025 ሁለተኛ ደረጃ ት/ትን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ለማድረስ የምታደርገው ጥረት ቢሳካም፤ የትምህርት ስርአቱ ካልተለወጠ በስተቀር፤ አሁን ባለው የትምህርተ ስርአት ወደሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገቡት ተማሪዎች፤ ወደከፍተኛ ት/ት ለመግባት የሚያስችላቸውን የቅድመ ት/ት ዝግጅት ለመወጣት የሚያስችል ብቃት ይዘው አይወጡም ሲል ጥናቱ ስጋቱን ይገልጻል።

አሁን ባለውና እስከ 2025 እንደሚቆይ በታሰበው የትምህርት ስርአት መሰረት፤ በኢትዮጵያ 80 ከመቶ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ወደ ሙያና ቴክኒክ ት/ት፤ 20 ከመቶ የሚሆኑትን ደግሞ ወደ ከፍተኛ ት/ት ይገባሉ ተብሎ ይታሰባል።

ይሁን እንጂ የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት መልቀቀቂያ ውጤቶች እነደሚያሳዪት ከሆነ፤ አብዛኛዎቹ የ10ኛ ክፍል ተመራቂዎች፤ ለከፍተኛ ት/ትም ለቅድመ ከፍተኛ ትምህርትም የሚያዘጋጃቸውንና የትምህርት ስርአቱ የሚጠይቀውን ብቃት ሳይዙ ት/ት ይጨርሳሉ ሲል ሪፖረቱ ጠቅሷል።

የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ለጠቅላላ ኢትዮጵያዊያን ይዳረስ ከተባለ ደግሞ፤ ባንድ በኩል  ተማሪዎች 10ኛ ክፍል ሲጨርሱ መሰረታዊ የከፍተኛ ትምህርት ብቃት ስለማይጨብጡ መወዳደር ስለማይችሉ ሞራላቸው የሚነካ ሲሆን፤ በሌላም በኩል ደግሞ ተማሪዎቹን ብቃት ባለው መልኩ በማይሰለጥኑበት ሁኔታ አገሪቱ ያሰላትን ወድ ሀብት ታባክናለች ሲል ሪፖርሩ አብራርቷል።

በጣም ወሳኝ የሆነው የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ ምርጫ ሊሆን የሚገባው፤ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ብቃት መመዘን ያለብን፤ አንደና ለከፍተኛ ት/ት ባላቸው ዝግጁነትና በችሎታቸው መጠን ሊማሩ በሚችሉበት ብቃትና ተነሳሽነት ሲሆን፤ ሁለተኛም ትምህረቱ ምን ያህል ህብረተሰቡን ሊጠቅም ይችላል በሚለው ነገር ላይ ነው ሲል ሪፖርቱ መክሯል።

ይህ በአገሪቱ የሰው ሀብት ልማት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ስላለውና አገሪቱ ወደመካከለኛው ገቢ ያላቸው አገሮች ተርታ የመግባት እድሏም በዚህ ስለሚወሰን፤ ፖለቲከኞች መምህራን፤ የልማት ሰራተኞች፤ ምሁራንና ሁሉም የጉዳዩ ባለቤቶች በዚህ ጉዳይ ላይ ሊመክሩበት ይገባል ሲል ሪፖርቱ ጥሪ አቅርቧል።

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s