ለፓትርያርክ መርቆሬዎስ እና ለአቃቤ መንበረ-ፓትሪያርክ ለአቡነ ናትናኤል የተማጽኖ ደብዳቤ ተጻፈ

ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ምዕምናን ዓለም አቀፍ ማህበር፤ ለፓርትያርክ አቡነ መርቆሪዎስና፤ ለአቃቤ መንበር አቡነ ናትናኤል የተማተፅኖ ደብዳቤ ፃፈ።

የቤ/ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲጠበቅ ሁለቱም ወገኖች ያስተላለፉትን ውግዘት ያለቅድመ ሁኔታ እንዲያነሱም ጠይቋል።

ዋና መቀመጫወን በአሜሪካ ያደረገው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን መዕመናን ዓለም አቀፍ ማሕበር፤ በቦርድ ሰብሳቢው በአቶ ይስሐቅ ክፍሌ ስም ባወጣው መግለጫ፤ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት በነበሩባተ ወቅት የተጀመረው የሽምግልና ጥረት ጥሩ መስመር ሲይዝ መቆየቱን አስታውሷል። ይህም መልካም ፍፃሜ እንዲያገኝ ሁሉም ወገኖች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

ሁለቱም ወገኖች ወግዘቱን እንዲያንሱ በአዲስ አበባ የሚገኙት አባቶች የሰላምና አንድነቱ ጉዳይ መፍትሄ እስኪያገኝ ፓትሪያርክ ከመምረጥ እንዲታገሱ ጥሪ አቅርቧል።

ብፁዕ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ መንበራቸው የመመለሳቸው ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ መንግስትም በዚህ ረገድ ይሁንታ እንዲሰጥ የምዕመናኑ ዓለም አቀፍ ማህበር ጥሪ አቅርቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አባቶች መካከል ዕርቅ እንዲመጣ ጥረት ሲያደርጉ ከቆዩት አንጋፋ ኢትዮጲያን አንዱ የሆኑት፤ የሊቀ ማዕምራን አበባው ይግዛው የቀብር ስነስርዓት፤ በትናንት እለት በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤ/ክ ተፈፅሟል።

የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን ለረዥም ግዜ የሰሩትና በተለያዩ መንግስታዊ ሃላፊነት ላይ ያገለገሉት ሊቀመምዕራን አበባው ይግዛው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፤ ባለፈው ሳምንት ሲሆን ሕይወታቸውም ያለፈው ለረዥም በስደት በሚኖሩባት ብርታኒያ ለንደን ነበር

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Ethiopia news. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s