የደቡብ ጎንደር እስቴ መካነ ኢየሱስ ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ ገቡ

መስከረም ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባና ግድያ ጭምር የተፈጸመባቸው  የደቡብ ጎንደር እስቴ መካነ ኢየሱስ ከተማ  ነዋሪዎች አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ ገቡ።ኢሳት  በቅርቡ እንደዘገበው፤በእስቴ መካነ ኢየሱስ ነዋሪዎችና በፖሊሶች መካከል ችግር የተፈጠረው፤በከተማዋ የሚያልፈው የመንገድ ፕሮጀክት በሌላ በኩል በማለፉ ምክንያት ህዝቡ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃወሞውን ለማሰማት በመውጣቱ ነው።

ለህዝቡ የታውሞ ሰልፍ የመንግስት ተወካዮች ምላሽ እንሰጣለን  ባሉት መሰረት የአካባቢው ነዋሪ  ቀና ምላሽ እየጠበቀ ባለበት ሁኔታ  ነበር – መንግስት ያሰማራው ልዩ ሃይል፦  ሰልፈኛውን ህዝብ በጅምላ ወደመደብደብ የተሰማራው።

የፖሊስ አባላቱ መውሰድ የጀመሩት ድንገተኛ የሀይል እርምጃ ህዝቡን በማስቆጣቱም ረብሻና ግርግሩ እየተባባሰ መጣ።በዚህ ጊዜ ፖሊሶቹ ወደ ሰልፈኛው ጥይት ተኮሱ።

እንደ ኢሳት ወኪል ዘገባ፤ በፖሊስ ጥይት የሞቱ እና የቆሰሉ ጥቂት አይደሉም።

የአካባቢው ፖሊስም ሆነ መንግስት፤ እንኳን ስለሞቱት ሰዎች ቀርቶ ተከስቶ ስለነበረው ክስተት ምንም ነገር አለማለታቸው ህብረተሰቡን ይበልጥ አበሳጭቶት እንደነበር በጊዜው  ተጠቁሟል።

በተለይ የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው በተባሉት የከተማዋ ወንዶች ላይ ከፍተኛ የሀይል እርምጃ በመወሰዱና እየተፈፀመባቸው ያለው ድብደባና አፈና ሊገታ ባለመቻሉ፤ አብዛኞቹ ወንዶች አካባቢያቸውን ለቅቀው ተሰደዋል ።

ስለተከሰተው ችግርም ሆነ ፖሊስ በህዝብ ላይ ስለወሰደው  የጭካኔ እርምጃ  በመገናኛ ብዙሀን ባይዘገብም፤ ወሬው በከተማዋ ዙሪያ  ወዳሉ ወረዳዎች  በስፋት  እየተዛመተ እና ችግሩ ይበልጥ እየተባባሰ እንደሆነ መዘገባችን ይታወሳል።

እየተፈፀመባቸው ባለው የጅምላ ድብደባና እየተወሰደባቸው ባለው የከፋ እርምጃ ግራ የተጋቡት የከተማዋ ነዋሪዎች ፦”የመንግስት ያለህ!የህግ ያለህ!>  እያሉ አቤቱታቸውን ለፌዴራል መንግስት ለማሰማት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሪፖርተር ጋዜጣ በእሁድ እትሙ እንደዘገበው፤የመንገድ ግንባታ ወደሌላ አቅጣጫ በመቀየሩ ምክንያት የተበሳጩ የደቡብ ጎንደር ነዋሪዎች፣ ቅሬታቸውን በቅርቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር ሆነው  ለተሾሙት አቶ ደመቀ መኮንንና ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች አቀረቡ ብሏል።

ነዋሪዎቹ በ2000 ዓ.ም. በአማራ ክልል ከሞጣ እስከ ደብረ ታቦር ድረስ መንገድ ይገነባል ተብሎ በመንግሥት ተነግሯቸው እያለ፣ በ2004 ዓ.ም. መጨረሻ የዚህ መንገድ ግንባታ ቀርቶ በሌላ አቅጣጫ ይገነባል በመባላቸው ተበሳጭተዋል ነው ያለው- ጋዜጣው።

ቀድሞ የተያዘው እቅድ ቀርቶ በሌላ አቅጣጫ መንገዱ እንዲገነባ ጨረታ መውጣቱን የሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለክልሉ መንግሥትና ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ቢያቀርቡም ፤በሁለቱ አካላት ምላሾች ባለመርካታቸውም፤ ነዋሪዎቹ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሁለት አውቶብሶች ሞልተው አዲስ አበባ ገብተዋል-ብሏል-ጋዜጣው።

ይሁንና ስለተፈጸመባቸው የሀይል እርምጃ ጋዜጣው ያለው ነገር የለም።
ለ አቤቱታ አዲስ አበባ የገቡት የእስቴ መካነ ኢየሱስ ከተማ ነዋሪዎች ከአዲሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ከአቶ ደመቀ መኮንን እና  ከመንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር  ከአቶ በቀለ ንጉሴ ጋርም መወያየታቸው ተመልክቷል።

‹‹አቶ ደመቀ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሚቀጥለው ሰኞ ወደ አካባቢው መጥተው በጉዳዩ ላይ በሰፊው ለመነጋገር ቀጠሮ ሰጥተውናል፤››ብለዋል-የከተማው ነዋሪዎች።

አዲሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በገቡት ቃል መሰረት በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ወደ ስፍራው በማቅናት በዛሬው ዕለት ነዋሪዎቹን ስለማወያየታቸው እስካሁን የደረሰን መረጃ የለም።

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Ethiopia news. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s