ከአንድ ሺ ያላነሱ ቤተሰቦች ጎዳና ላይ ተበተኑ

መስከረም ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ መስተዳዳር በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዜሮ አንድ ሱቂ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከመስከረም 19  ጀምሮ እያካሄደ ባለው ህገወጥ ያላቸውን ቤቶች በማፍረስ እርምጃ ከ1000 ያላነሱ ነዋሪዎችን የያዙ  ከ130 በላይ ቤቶች እየፈረሱ ነው።በመንግስት ድርጊት በርካታ ህጻናት ሲያልቅሱ፣ ቋሚዎች ሙታንን ለመቅበር ሲቸገሩ፣ አሮጊቶችና ሽማግሊዎች መጠጊያ አጥተው ለብርድና ለዝናብ መዳረጋቸውን ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት ገልጠዋል።

አቶ ፍቃዱ ማንደፍሮ እንዳሉት 50 የሚሆኑ ፖሊሶችና የጎዳና ተዳዳሪዎች በአካባቢው መጥተው ጉዳት እንዳደረሱባቸው ገልጠዋል

አቶ ፈቃዱ እንደሚሉት መንግስት በጻፈላቸው  ትብብር በግላቸው የመሰረተ ልማቶችን መዘርጋታቸውን ገልጸዋል

ሌላው ተፈናቃይ አቶ አለሙ በንቲ በበኩላቸው በርካታ ህጻናቶችና አራሶች ሳይቀሩ ውጭ እያደሩ ነው መሆኑን ተናግረዋል

አቶ ወርቁ ማተቤ በበኩላቸው የሚደርስባቸውን በደል “ቤታችንም ሰውነታችንንም” ማዳን አልቻልንም በማለት ይገልጡታልአቶ አለሙ እርሳቸው በሚኖሩበት አካባቢ መንታ ወልደው ሜዳ ላይ የተጣሉ እናቶች መኖራቸውን በሀዘን ተናግረዋል

በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ መስተዳድር ሃለፊዎችን ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካልንም።

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s