ዲፕሎማቶች በዋናነት የሚገመገሙት በአመለካከት መሆኑ ታወቀ

Sept. 14) ከአዲሱ 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ሰራተኞችና፤ ኢትዮጵያን ወክለው በውጭ አገራት የሚገኙ ዲፕሎማቶች ግምገማ፤ 60 ከመቶ አመለካከት 40 ከመቶ ደግሞ ሥራ ይሆናል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ምንጮቻችን ገለፁ።

ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን እንደገለፁት ከሆነ ከያዝነው አዲስ አመት ጀምሮ በውጭ አገር የሚገኙ ዲፕሎማቶች የሚገመገሙት፤ ከምርጫ 97 በፊት እንደነበረው ከሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤት በሚመጣ መገምገሚያ ቅጽ ሳይሆን፤ ምርጫ 97ን ተከትሎ በነበሩት አመታት እንደነበረው፤  60 ከመቶ ለኢህአዴግ ፖሊሲ ባላቸው አመለካከት እንደሚሆን ታውቋል።

አዲሱ የግምገማ ደንብ በ2005 ይተገበራል ቢባልም የምክትል አምባሳደርነት ደረጃ ያላቸው ዲፕሎማቶች ከወዲሁ ብቃት ያንሳቸዋል በሚል ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ከተጠሩ ወር ከ20 ቀን እንዳለፋቸውና፤ ለሥርዓቱ ቅርበትና ታማኝነት ካላቸው ዲፕሎማቶች በስተቀር እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ እንደሌለሉ ምንጮቻቸን ጠቅሰዋል።

ባለፉት ሳምንታት አያሌ ዲፕሎማቶች በተላኩበት አገር ወይም ወደሌላ ሦስተኛ አገር ስደተኝነት በመጠየቅ እንደቀሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፤ በእነሱ ምትክ ሌሎች ዲፕሎማቶችን ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና፤ ባለፈው ሰኔ ወር የፀደቀ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀ “ልማታዊ የዲፕሎማሲ ሠራዊት የንቅናቄ ሰነድ” የተሠኘ ባለ 49 ገጽ ሠነድ፤ በእጃችን የገባ ሲሆን ሰነዱ ዲፕሎማቶችን፤ የፖለቲካ አመራር ሰጪውን ድርጅት (ኢህአዴግ) መዋቅር በያዘ መልኩ እንዲዋቀሩ ማድረግ አላማው እንደሆነ ይናገራል። በሰነዱ ዙሪያ ከዲፕሎማቶች ጋር ሰፊ ውይይትና ዝግጅት እንደምናደርግ ከወዲሁ እንገልፃለን።

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s