የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት በመከላከያ ውስጥ ያለውን ቅሬታ ተጠቆመ

መስከረም ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት ማክሰኞ ዕለት የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት ከብሔራዊ ተዋጽኦ አንጻር በመከላከያ ውስጥ ያለውን የቆየ ቅሬታ ማባባሱን ምንጮች ጠቆሙ፡፡

ትላንት ከሕመማቸው በማገገም ላይ ባሉት ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት 34 የመከላከያ ኮሎኔሎችን ወደ ብርጋዴር ጄኔራል ያሳደገ ሲሆን ከነዚህ ሹማምንት መካከል ከግማሸ በላይ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮች መሆናቸው ከብሔር ተዋጽኦ አንጻር ወትሮም የነበረውን ውጥረት እንዳባባሰው ምንጫችን ጠቁመዋል፡፡

በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ አመራሩን የተቆጣጠሩት የህወሃት ታጋዮች መሆናቸው ለረዥም ጊዜ ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረ ጉዳይ ከመሆኑም በላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የነበሩት ሟቹ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ችግሩን ለመፍታት አለመሞከራቸው በሰራዊቱ ውስጥ የጎሰኝነት ስሜት ሥር ሰዶ እንዲቆይ ምክንያት መሆኑን ምንጫችን አስረድቶአል፡፡ በዚህም ምክንያት በሠራዊት ውስጥ ዋንኛ መለያ ማዕረግ ወይም የሥራ ብቃት ሳይሆን ጎሳ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ሰራዊቱ አሁን ድረስ “እሱ እኮ ህወሃት ነው፣እገሌ ብአዴን ነው…”በሚል የሚታወቅበት አሳዛኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፤ ይህ ደግሞ ወቅቱን ጠብቆ መፈንዳቱና ዋጋ ማስከፈሉ እንደማይቀር ምንጫችን ተናግረዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትር ባልተሰየመበት ሁኔታ ተጣድፎ ለመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ብቻ ሹመት መስጠቱ አዲሱ የአገሪቱ አመራር የሰራዊቱን ድጋፍ ከወዲሁ ለማግኘት የታለመ ሳይሆን እንደማይቀር የጠቆሙት ምንጫችን ይህ እርምጃ የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችን ብቻ መጥቀሙ ግን መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሩን ጨምሮ በርካታ የሠራዊቱን አባላት ማስከፋቱ ሌላ ችግር ሆኖ ብቅ እንዳይል ሥጋቱን ገልጻል፡፡

በጀኔቭ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የአሜሪካ መንግስት ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዳግላስ ከአመታት በፊት ይህን ሀቅ በመግለጣቸው በ አቶ መለስ ፦”ኢዲየት” ተብለው መሰደባቸው አይዘነጋም።
በግንቦት ወር 2004 ዓ.ም አጋማሸ ከእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ሪቻርድ ዳውደን ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት አቶ መለስ ዜናዊ ለመጀመሪያ ጊዜ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ባለው የብሔር ተዋጽኦ የቀድሞ የህወሃት ታጋዮች እንደሚበዙ በይፋ ማመናቸው የሚታወስ ነው፡፡አቶ መለስ እንዳሉት “ሠራዊቱ በብሔር ተዋጽኦ ረገድ በተሻለ ደረጃ ላይ ቢገኝም አመራሩ
ግን ከህወሃት የቀድሞ ታጋዮች ተጽዕኖ አልጸዳም” ብለዋል፡፡

ሰሞኑን የማእረግ እድገት ከተሰጣቸው 37 መኮንኖች መካከል  23 የትግራይ ተወላጆች የሆኑ የህወሀት አባላት ሲሆኑ፤ቀሪዎቹ 13ቱ ደግሞ ከልዩ ልዩ ብሔረሰቦች የተውጣጡ ናቸው።

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ከነበሩት ወደ 60 የሚጠጉ ጀነራሎች 58ቱ የትግራይ ተወላጆች እንደሆኑ የግንቦት 7 ራዲዮ ከነ ስማቸው እና ከያዙነት ሀላፊነት ጭምር በዝርዝር ማቅረቡ ይታወሳል።

የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ወደ ሥልጣን እየመጣ ያለው አዲስ ቡድን ይህን ልዩነት በማጥበብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ የስልጣን ውክልና የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል በሚል በተለይ ምዕራባዊያን ተስፋ በጣሉበት ሁኔታ ትናንት የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት አሳፋሪና አስደንጋጭ ሆኗል።

ከኮሎኔልነት ወደ ብርጋዴር ጄነራልነት የተሾሙት 34ቱ  መኮንኖች በስማቸውና በብሔር ተዋጽኦዋቸው  ሲቀመጡ

ብርጋዴር ጄነራል ያይኔ ስዩም፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ጉዕሽ ፅጌ ፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ደግፊ ቢዲ – ብሔር ትግሬ ናቸው፡፡

ብርጋዴር ጄነራል ገብሩ ገብረሚካኤል፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ወልደ ገብርኤል ባቢ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ፍሰሃ ኪዳነ ማሪያም -ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ሀለፎም እጅጉ፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል አታክልቲ በርሄ ፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል አብረሃ አረጋይ፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ማዕሾ ሃጎስ፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ገብረመድህን ፍቃዱ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ፍስሃ በየነ፣ – ብሔር ትግሬ
ብርጋዴር ጄነራል ገብረኪዳን ገብረማሪያም፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ጥጋቡ ይልማ – ብሔር ትግሬ
ብርጋዴር ጄነራል አስራት ዶኖይሮ – ብሔር ቅይጥ
ብርጋዴር ጄነራል መሸሻ ገብረሚካኤል፣ – ብሔር ትግሬ
ብርጋዴር ጄነራል አብርሃ ተስፋዪ፣ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል አስካለ ብርሃነ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል የማነ ሙሉ – ብሔር ትግሬ
ብርጋዴር ጄነራል ሙሉ ግርማይ – ብሔር ትግሬ

ብርጋዴር ጄነራል ዘውዱ በላይ – ብሔር ትግሬ
ብርጋዴር ጄነራል አሰፋ ገብሩ – ብሔር ትግሬ
ብርጋዴር ጄነራል ታረቀኝ ካሳሁን – አማራ

ብርጋዴር ጄነራል ሹማ አብደታ – አማራ

ብርጋዴር ጄነራል ይመር መኮንን – አማራ

ብርጋዴር ጄነራል ከድር አራርሳ – ኦሮሞ
ብርጋዴር ጄነራል ድሪባ መኮንን – ኦሮሞ
ብርጋዴር ጄነራል ደስታ አብቺ – ኦሮሞ

ብርጋዴር ጄነራል ዱባለ አብዲ – ኦሮሞ

ብርጋዴር ጄነራል ኩምሳ ሻንቆ፣ – ደቡብ ህዝቦች
ብርጋዴር ጄነራል አጫሉ ሸለመ – ደቡብ ህዝቦች
ብርጋዴር ጄነራል አቤል አየለ – አልታወቀም
ብርጋዴር ጄነራል ኩመራ ነጋሪ፣ – አልታወቀም

ብርጋዲየር ጀነራል ይብራህ ዘሪሁን-አልታወቀም

ከብርጋዲየር ጀነራልነት  ወደ ሜጀር ጄነራልነት ያደጉት ሦስቱ ገድሞ፦

ሜጀር ጄነራል መሰለ በለጠ – ብሔር ትግሬ
ሜጀር ጄነራል መሐሪ ዘውዴ – ብሔር ትግሬ እና
ሜጀር ጄነራል ሐሰን ኢብራሂምና – ብሔር ትግሬ   ናቸው።

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Ethiopia news. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s