ወቅታዊ ዜና:- ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፖሊስ አባላት ጋር ተጋጩ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፖሊስ አባላት ጋር ተጋጩ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል

በዛሬው የኢድ አል ፈጥር በአል ላይ በጊዮን ሆቴል በኩል የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰሙ ሲሄዱ የነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፣ ከብረት ለበስ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ጋር ተጋጭተዋል። በርካታ ሙስሊሞች ተረጋግጠዋል፣ በቆመጥና በዱላ ተደብድበዋል፤ የተፈነከቱ፣  እጅና እግራቸው የተሰባበሩ ሰዎች ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል። አንዲት እርጉዝ ሴት መረገጧንም ዘጋቢያችን ገልጧል። ብዙዎችም በፖሊስ ካሚዮን ተጭነው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።

ድርጊቱ ያበሳጫቸው ወጣቶች በድንጋይና በአካል ከፖሊስ ጋር ግብግብ ፈጥረው በብዙ ፖሊሶች ላይ ጉዳት አድርሰዋል። እስካሁን ምን ያክል ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ እና ምን ያክሉ እንደታሰሩ በቁጥር ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። የአይን እማኞች እንዳሉት ጉዳቱ ያየለው በህጻናት፣ ሴቶች እና ሽማግሌዎች ላይ ነው።

Source;ESAT

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s