ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሀይማኖታዊ ጽሁፎቹ የሚታወቀው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የአቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ እረፍት እንዳስደነገጠው ገልጧል::
በአቡነ ጳውሎስ የ20 አመታት አስተዳዳር የተሰሩ መልካም ስራዎች የመኖራቸውን ያክል ባይሰሩ ይሻል ነበር የሚያስብሉ ጉዳዮች እንደነበሩም ዲያቆን ዳንኤል ይናገራል::
ወቅቱ የመረጋጋት ፣ እርስ በርስ የምንተጋገዝበት እና ለወደፊቱ መልካም የሆኑ ስራዎችን ስርተን ለማለፍ የምንችልበት መሆኑን ሁለም ሰው ልብ ሊለው እንደሚገባ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መክሯል::
Advertisements