ሰራዊቱ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ ነው

የአቶ መለስ ዜናዊን መሰወር ተከትሎ በኢትዮጵያ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፤ ጦር ሰራዊቱ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ እንዲቆም የታዘዘው፤ በቅርቡ በተመሰረተውና በጦር ሰራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ውይይት በጫረው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ (ነኢሰን) መግለጫ ጭምርም እንደሆነ አስተማማኝ የውስጥ ምንጭ ገለጸ።
ለመከላከያ ሚኒስቴር ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተመሰረተበትን መግለጫ የበተነው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ፤ ከተመሰረተ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ ውይይት እንደጫረና፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አለመኖር ታክሎበት ስጋት በመፍጠሩ ምክንያት፤ አየር ሀይሉን ጨምሮ የጦር ሰራዊቱ በሙሉ በአንደኛ ደረጃ በተጠንቀቅ እንዲቆም መደረጉ ታውቋል።
ባለፈው ሳምንት እንደዘገብነው፤ ለሰራዊቱ የአደገኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው፤ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ሊሰነዝሩ ስለመዘጋጀታቸው፤ መረጃ ደርሶናል በሚል ሰበብ ቢሆንም፤ የጦር ባለሙያዎች ለአክራሪዎች ጥቃት የአየር ሀይል በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ መቆም አሳማን አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
ለኢሳት ባለፈው ሳምንት በደረሰው መረጃ መሰረት፤ በዘመቻ መምሪያና በድርጅት መምሪያ ያሉ ከፍተኛና መስመራዊ መኮንኖች፤ 24 ሰኣታት ቢሮዎቻቸውን ክፍት አድርገው፤ በየተራ የበላይ ትእዛዝ እንዲጠባበቁ እንደተነገራቸው መዘገባችን ይታወሳል።

Source; ESAT

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Ethiopia news. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s