“አገሪቷ በማን እየተመራች እንደሆነ አለመታወቁ አሣስቦኛል” ሲል መኢአድ ስጋቱን ገለጸ

ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአሁኑ ጊዜ አገሪቷን እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ናቸው መባሉ እንዳልተዋጠለት እና በትክክል ይች አገር በማን እየተመራች እንደሆነ አለመታወቁ እንዳሣሰበው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ገለጸ።“አገሪቷ በማን እየተመራች እንደሆነ አለመታወቁ አሣስቦኛል” ሲል መኢአድ ስጋቱን ገለጸ

ይህ የመኢአድ  ስጋት የተገለጸው፤ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህይወት እንደሌሉ የሚያመላክቱ ዘገባዎች እየወጡ ባሉበት ባሁኑ ጊዜ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን ፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና አሁንም የአገሪቱ መሪ እርሳቸው እንደሆኑ በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

መኢአድ እንዳለው፦ አገሪቱን እየመሩ ያሉት አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው ተብሎ መገለፁ፤ የህገመንግስቱን የህግ ክፍተት የሚያሳይ ነው።

“የኢትዮጵያ ህዝብ መሪው ሲታመምና ሳይኖር በማን እንደሚመራ የማወቅ መብት አጥቷል” ያሉት የፓርቲው አመራሮች፤ በአሁኑ ጊዜ አገሪቱን ማን እንደሚመራትም አናውቅም፡፡”ብለዋል።

የመ ኢአድ አመራሮች አክለውም፦” የጠ/ሚኒስትሩ ሥራ ደቂቃ በደቂቃ ውሳኔ የሚጠይቁና ፊርማ የሚያስፈልጓቸው ጉዳዮች አሉበት፡፡ አቶ በረከት ማነው የሚመራን ተብለው ሲጠየቁ ፤<ሆስፒታል የተኙት አቶ መለስ ናቸው> ማለታቸው ፤ የህገመንግስቱን የህግ ክፍተት የሚያሳይ ነው፡፡ ክፍተቱ፤ምክትል ጠሚኒስትሩ ተክተው የመሥራት ሥልጣን እንደሌላቸው ያሳየ ነው። ስለሆነም  በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ የሚመራውን አያውቅም” ብለዋል።

በሌላ በኩል መንግስት እጁን ከሃይማኖት ላይ እንዲሰበስብ ጥሪውን መኢአድ ጥሪ ማቅረቡን የፍኖተ-ነጻነት ዘገባ ያመለክታል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ወንድምአገኝ ደነቀው፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ ወይዘሪት መሶበ ወርቅ ቅጣው እና  የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ አበባው መሐሪ በጋራ በመሆን በሰጡት በዚሁ  መግለጫ፤-“ የኢህአዴግ መንግስት የሃይማኖት ተቋማትን በካድሬዎች ለመምራት ካለው  አቋም በመነሳት እጁን በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ አስገብቶ ሃይማኖቶችን እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚያከናውነውን ተግባር ማቆም አለበት” ብሎአል፡፡

 

“በአገሪቱ ውስጥ አሸባሪነት ስለመኖሩ ማረጋገጫ የለም” ያሉት የመኢአድ አመራሮች፤ “የሙስሊሙን ህብረተሰብ ለመከፋፈል መንግስት እያከናወነ ያለውን ድርጅታዊ ሥራ ማቆም አለበት” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የመኢአድ አመራሮች አያይዘውም፦ “ኢህአዴግ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ላነሳው ጥያቄ ፦” መሪዎቻችሁን በቀበሌ ምረጡ” የሚል መልስ መሰጠቱ፤በግልጽ መንግስት በሙስሊም ሃይማኖት ውስጥ ለመዘርጋት የፈለገውን እጅ የሚያሳይ ነው” ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በዋልድባ ገዳም ሦስት ቤተክርስቲያኖችን ለማፍረስ መወሰኑ እና  ምዕመናን በሃይማኖቱ ሥርዓት መሠረት ዓመታዊ ክብረበዓል እንዳያከብሩ መከልከሉ ፤ ኢህአዴግ በሃይማኖት ዙሪያ እየተከተለ ያለውን ጣልቃ ገብነት የሚያሳይ ነው፡፡” ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል-የመኢአድ አመራሮች።

Advertisements

About Legesse Habtegiorgis

I wish to see democratic ethiopia.
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s